የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

 

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርአት ተካሄደ።

የፋብሪካው ግንባታ በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚከናወን ሲሆን በሀገሪቱ ያለውን የሲሚንቶ እጥረት ሊቀርፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

(በሃኒ አበበ)