የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ተደራሽ ለማድረግ አመራሩ የበኩሉን ሊያበረክት እንደሚገባ ተገለፀ

የካቲት 21/2013 (ዋልታ) የማህበረሰብ አቀፍ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ በድሬዳዋ ከተማ ተካሄደ ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ የማህበረሰብ አቀፍ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደረግ በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ  በጤናና አካል በቃት እንቅስቃሴ ስፖርት መሳተፍ አለበት ብለዋል፡ ፡

በድሬደዋ ከተማ  በተካሄደው 3ኛው ሀገር አቀፍ የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ  እንቅስቃሴ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጆሃርን ጨምሮ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ አካል ጉዳተኞችን ፣ ህፃናት እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተሳተፉበት ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡