የማህጸን በር ካንሰርን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – የማህጸን በር ካንሰርን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አሳሰበ፡፡

ቢሮው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የእናቶችን ማህጸን በር የቅድመ ካንሰር ልየታ እና የህክምና አገልግሎት የንቅናቄ ፕሮግራም አስጀምሯል፡፡

ንቅናቄው እድሜያቸው ከ30 እስከ 49 አመት ያሉ ሁሉም እናቶችን በመለየት የህክምና አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን ለውጤታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ከ130 በላይ ጤና ተቋማት መዘጋጀታቸውም ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡