የቀድሞው የኢህዴሪ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈፀመ

የቀድሞው የኢህዲሪ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከጳጉሜን 5 ቀን 1979 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 1982 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የተወለዱት ሐምሌ 7 ቀን 1937 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለምዶ ቀጨኔ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው።

በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች አገራቸውን ያገለገሉት ፍቅረሥላሴ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ (ኢሰፓ) አደራጅ ኮሚቴ እና የደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።

“እኛና አብዮቱ እና እኔና አብዮቱ” በሚል ርዕስ ሁለት መጽሐፍት ጽፈው ለአንባቢያን አድርሰዋል።

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የሁለት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት እንደነበሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።