የብላቴ ኮማንዶ አየር ወለድ ኃይል ማሰለጠኛ ማዕከል አመራሮችና አባላት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ አደረጉ

ሚያዝያ 18/2014 (ዋልታ) የማሰልጠኛ ማዕከሉ አባላት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት ቤተሰቦች እና በጨርቾ ቀበሌ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የገንዘብና የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የማዕከሉ ም/አዛዥ የሰው ሃብት ልማትና አገልግሎት ሌ/ኮ መንገሻ ምንደሲል እንደተናገሩት ከህዝብ አብራክ የወጣን የህዝብ ልጅ እንደመሆናችን፤ ህዝባዊ ባህሪያችን ተላብሰን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ድጋፉን አበርክተናል። በቀጣይነትም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አለኝታነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በሠጡት አስተያየት የመከላከያ ሰራዊቱ ርህሩህና ታማኝ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን ገልፀው በተደረገላቸው ድጋፍም ደስተኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡