የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን የሥራ አፈፃፀም የግምገማ እያካሄደ ነው

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን የ2013 በጀት ዓመት የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የፓርቲው መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮች በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመሩ የጎላ ሚና ይጫወታል ነው የተባለው፡፡

ጠንካራ የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት የቁጥጥር እና ኢንስፔክሽን ወሳኝ መሆኑን ኮሚሽነር ኢንጂነር አወቀ ኃይለማሪያም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ኮሚሽኑ የ6 ወር ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም የራሳቸውን ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ፓርቲው በአሁኑ ሰዓት 9 ሚሊየን 941 ሺህ 467 አባላት እና አመራሮች በመላ አገሪቱ እንዳሉት በመግለፅ እነዚህ አባላት በዳታ ቤዝ መመዝገብ እንዳለባቸው አስታውሷል፡፡

የውይይት መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል፡፡

(በሳሙኤል ሀጎስ)