የብልፅግና ፓርቲ ችግሮችን በማለፍ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው – የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አደም ፋራህ

አደም ፋራህ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ በለውጡ ሂደት በርካታ ፈተና ቢያጋጥሙትም ችግሮችን በማለፍ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከፈተና ወደ ልዕልና በሚል መሪ ዓላማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ በጉባዔው የፓርቲው አመራሮች የሚሰሩት ሥራ በጥራት እንዲያከናውኑ አቅጣጫ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

የተጀመረው አገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተለያዩ ሥራዎች ፓርቲው እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ለዛሬና ለነገ ትውልድ የሚለፋ ፓርቲ ነው ያሉት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አደም ፋራህ መፍትሔ ተኮር ፓርቲ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው ጉባኤ በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተደቀነውን ፈተናዎች በመቀልበስ የሚካሄድ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ጉባኤው ፓርቲውን በአመራር፣ በአደረጃጀትና በአሰራር በማጠናከር የጀመረውን አገራዊ ለውጥ በማፅናት ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረውም አስረድተዋል፡፡

በሱራፌል መንግሥቴ እና ሳሙኤል ሓጎስ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW