የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤ ከመጋቢት 2 እስከ 4 እንደሚካሄድ ተገለጸ

አደም ፋራህ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤ ከመጋቢት 2 እስከ 4/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ መጠናቀቅን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

“ታሪካዊ” ያለውን የመጀመሪያ ጉባኤን ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁንና ጉባኤው “ከፈተና ወደ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ጉባኤ ፓርቲውን በብቃት የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎችን መምረጥና የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ዋና ዓላማው ስለመሆኑም አንስተዋል።

በደምሰው በነበሩ