የትንሣዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው


ሚያዝያ 24/2013 (ዋልታ) –
የትንሣኤ በዓል በመላው ሀገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለሊቱን የተለያዩ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች ተከናውነዋል።

የትንሳዔን በዓል ስናከብር የተቸገሩ እና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ የሀይማኖት አባቶች አሳስበዋል።