የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ዮሺሮ ሞሪ ከሃላፊነት ለቀቁ

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ዮሺሮ ሞሪ

የካቲት 05/2013 (ዋልታ) – የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ዮሺሮ ሞሪ ከሃላፊነት ለቀቁ፡፡

የ83 አመቱ አዛውንት ከዚህ በፊት ”ሴቶች ብዙ ያወራሉ” ፤ “ሴት የቦርድ ሃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ ብዙ ጊዜ ይወስዳል” በማለት ሴቶችን ባልተገባ መልኩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በርካታ ትችት ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡

ወቀሳውን ተከትሎም ሃላፊው በይፋ ይቅርታ ጠይቀው እንደነበርም ይታወሳል፡፡

በወቅቱም ዋናው ነገር ኦሊምፒኩን በጊዜው ማዘጋጀት እንጅ የእርሳቸው ጉዳይ ለውድድሩ እንቅፋት ሊሆን እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሃላፊነታቸውን ከለቀቁ በኋላም ንግግራቸው አግባብ እንዳልነበር የተናገሩት ዮሺሮ ሞሪ ከንግግራቸው በኋላም ከቤተሰቦቻቸውም ከባድ ቁጣና ውግዘት ማስተናገዳቸውን ተናግረዋል፡፡