የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉ ተገለጸ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ 

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን እና አዲስ ዋጋ መዘጋጀቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዘርፉ ተሳታፊዎች ትርፍ ህዳግ እንዲሻሻል መንግስት በሰጠው ውሳኔ መሰረት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን በመከለስ አዲስ ዋጋ መዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ ለዋልታ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፡-

ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ67 ሳንቲም
ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ27 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም
ኬሮሲን በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም
ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 18 ብር ከ63 ሳንቲም
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 18 ብር ከ17 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 32 ብር ከ76 ሳንቲም መሆኑን የንግድና ኢንዱትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።