የአለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር በትግራይ ያለው የሰብአዊ ድጋፍ መሻሻሉን አስታወቁ

የካቲት 18፣ 2013 (ዋልታ) – የአለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሌይ በትግራይ ያለው የሰብአዊ ድጋፍ መሻሻሉን አስታወቁ።

ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ በትግራይ ተገኝተው ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር ተወያይተዋል። በዚህም በክልሉ የሚደረገው ድጋፍ እየተሻሻለ መምጣቱን ተረድተዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ በሰብአዊ ድጋፉ ላይ መሻሻሎች ያሉ ቢሆንም ቀሪ ስራዎች አሉ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በክለሉ የተጠናከረ ስራ ለማከናወን ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።