የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 1ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም ተከናወነ

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 1ኛ ሙት አመት መታሰቢያ ተከናወነ። በአርቲስቱ ስም የተራድኦ ድርጅት በይፋ ተመስርቷል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ አልበም “ማሊመሊሳ” በመታሰቢያ ስርዓቱ ላይ የተመረቀ ሲሆን የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዋች እና የስራ ባልደረቦች ተገኝተው ነበር።

አርቲስቱ በህይወት እያለ የሰራቸው የሙዚቃ ስራዋች ተሰብስበው  ለአድናቂዎቹ ቀርበዋል።

በአርቲስት አጫሉ  ሁንዴሳ ስም  የተጀመረው የተራድኦ ፋውንዴሽን በኪነጥበቡ ዘርፋ አክተዋፅኦ ያበረከቱ አንጋፋ አርቲስቶች የሚደጎሙበት፣ ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያውች የሚበረታቱበት ፣በስራቸው አመርቂ ውጤት ያመጡ ደግሞ  የሚሸለሙበት መሆኑ ተነግሯል።

(በቁምነገር አህመድ)