የአውሮፓ ኅብረት ለኢጋድ አባል ሀገራት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 29/2013 (ዋልታ) – የአውሮፓ ኅብረት ለኢጋድ አባል ሀገራት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ከተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የኮቪድ-19 ምላሽ የሚያግዙ ከ13 ሚሊየን ዩሮ በላይ የሚያወጡ የሕክምና መገልገያ መሳሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት እና ኢጋድ የኮቪድ-19 የሚያሳድረውን የጤና እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ላይ የሚሰጡት ምላሽ አካል ነው ተብሏል፡፡
የኢጋድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መሳሪዎቹን ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ አስረክበዋል፡፡
የተደረጉ ድጋፎችም የግል የሕክምና ደህንነት መጠበቂያዎች፣ የፊት ማስኮች፣ አምቡላንሶች፣ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪ እና መሰል የህክምና ቁሳቁስ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል የሚሰራጩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ስርጭት ወደ ሀገር ውስጥ መግቢያ በሮች አከባቢ እና ድንበር ላይ ለሚገኙ የስደተኞች ካምፕ የሚሰራጩ ሲሆን፣ እንደ አጠቃቀማቸው ደግሞ በድጋሚ የሚሰራጭ መሆኑን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!