የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት ተፈረመ

 

የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።

ስምምነቱ የተፈረመው የዲዛይን ፣ የማማከርና የቁጥጥር አገልግሎቱን ከሚያከናውነው ዮናስ አባይ አማካሪ አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ ከተባለ ድርጅት ጋር ነው።

የዲዛይን ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ እንደሚያቀርብ ከኮሚሽኑ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

የዲዛይን ስራው የካፍ ስታንዳርድን ጠብቆ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።