የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የካቲት 25 2013 ዓም. (ዋልታ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በ8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሞ እና ልዩ ልዩ ሹመቶችንም አጽድቆ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡