የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ከምሁራን ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

ግንቦት 30/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ከምሁራን ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
ውይይቱ በኢትዮጵያ ለአስትሮኖሚ (ስነፈለክ) እና ለህዋ ሳይንስ ጥናት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን መለየትና ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
እንደ አገር የቴሌስኮፕ ምልከታ ቦታዎችን በማስፋፋት ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁማል፡፡

ስራ ላይ ከሚገኘው የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና የምርምር ማዕከል በተጨማሪ በቀጣዮቹ 1 ዓመታት 3 ተጨማሪ ማዕከላትን ለመገንባት ዕቅድ ተይዟል፡፡
በላሊበላ በሚገኙ 3 አካባቢዎች ቦታ መረጣ ተካሂዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን አንደኛው በቅርቡ ርክክብ ይካሄድበታል ተብሏል፡፡
በቀጣይም በደቡብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ሌሎች ማዕከላትን ለመገንባት ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው፡፡
የስነ ፈለክና የህዋ ሳይንስ ጥናት ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)