የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ ካኖ ልዩ በረራ ጀመረ

ሚያዝያ 04/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ አዲስና ልዩ በረራ ጀመረ።
አየር መንገዱ የመጀመሪያውን በረራም እ.አ.አ ሚያዝያ 06 ማድረጉን አረጋግጧል፡፡
በናይጄርያ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሽመልስ አራጌ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማላም አሚኑ ካኖ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ (ማኪያ) ልዩ በረራውን እያስፋፋ ይሄዳል።
አየር መንገዱ በማኪያ በረራ ከሚያደርጉ አየር መንገዶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ ወደ ስፍራው የሚበር ብቸኛ የዓለም ዓቀፍ አየር መንገድ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማኪያ በተጨማሪ በኢኑጉ የአካኑ ኢቢያም ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የበረራ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ማስታወሳቸውን የናይጄሪያው ዘ ሰንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ውስጥ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው አየር መንገድ መሆኑ ይታወቃል።