የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

መጋቢት 30/ 2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ የጀመረበትን 75ኛ ዓመቱን እያከበረ ይገኛል፡፡

አየር መንገዱ ከ75 ዓመታት በፊት በ1938 ዓ.ም/በፈረንጆቹ 1946/ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ በረራ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በአስመራ አድርጎ ወደ ካይሮ በረረ።

አንጋፋው አየር መንገዱ በረራ የጀመረው ከተመሰረት ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዛሬው እለት 75ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።