የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በድምቀት ተጠናቋል – የጋራ ግብረ ኃይሉ

ሰኔ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) 1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በደመቀ እና ኃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

ግብረ ኃይሉ በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች የታደሙበት የኢድ ሶላት በዓሉን በሚመጥን ድምቀት ተከናውኗል ብሏል፡፡

ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ ትጋት ለፈጸሙ የፀጥታ አካላት፣ ለፀጥታ ሃይሉ ጋር ትብብር ላደረጉ የዕምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ለሰላም ወዳዱ የመዲናዋ ነዋሪ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይሉ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሠላም ፣ የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡