የእንግሊዙ ልዑል ፊሊፕ አረፉ

ሚያዝያ 01/2013 (ዋልታ) – የእንግሊዝ ንግስት ኤልሳቤጥ ባለቤት የነበሩት ልዑል ፊሊፕ በ99 ዓመታቸው አረፉ፡፡

ለ74 ዓመታት የብሪታኒያ ንግስት ኤልሳቤጥ ባለቤት የነበሩት እና ከንጉሣዊ ቤተሰብ የተገኙት ልዑል ፊሊፕ ዛሬ አርፈዋል፡፡

ልዑል ፊሊፕ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 2020 በቡድሃም ቤተመንግስት ውስጥ በወታደራዊ ሥነ-ስርዓት ላይ ታድመው ነበር::

ልዑሉ በልብ ህመም በሽታ የቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው በመጋቢት አጋማሽ ላይ ነበር ከሆስፒታል የወጡት፡፡