የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን የአምስት ስታዲየሞችን ዲዛይን አዘጋጀ

ግንቦት 24/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በክልሉ አምስት ስታዲየሞችን ለመገንባት የሚያስችል ዲዛይን አዘጋጅቶ አስረከበ።
የስታዲየም ዲዛይኖቹ ደምቢ ዶሎ፣ አምቦ፣ ፊቼ፣ ሀሮማያ እና አወዳይ ከተሞች የተዘጋጁ ሲሆኑ ለዚህም ከ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርኋል ነው የተባለው።
የስታድየም ዲዛይኑን የክልሉ ስፓርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ናስር ሁሴን ለከተማዎቹ ተወካዮች አስረክበዋል።
በርክክብ ስነ-ስርአት ላይ ኮሚሽነር ናስር ሁሴን የስታዲየሙ ግንባታ እውን እንዲሆን እና በታሰበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ መንግስት ድጋፍና ክትትል እንደሚያደረግ ገልፀዋል፡፡
በ5 ከተሞች የሚገነቡት ስታዲየሞች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆን ከ40ሺህ እስከ 50ሺህ ደጋፊዎችን ማስተናገድ ይችላሉ ተብሏል።
የስታዲየሞቹ ግንባታ በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ የስፓርት መሰረት ልማት ጥያቄዋችን ለመመለስ ያስችላልም ነው የተባለው።
(በመሰረት ተስፋዬ)