የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለእድለኞች ሽልማት አበረከተ

የአሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 2ኛውን ዙር “የይመንዝሩ፤ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ” መርኃግብር ለዕድለኞች የሽልማት አሰጣጥ ሥነሥርዓት አከናውኗል፡፡

በመርኃግብሩ ዘጠኝ የሚጠጉ ሽልማቶች ለዕድለኞች ተበርክቷል፡፡

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን ደንበኞች ከተለያዩ ሀገራ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሬ በባንኩ ስመነዝሩ የማበረታቻ ሽልማቶች እንደምበረከትላቸው ገልጸው፣ በቀጣይ በተለያዩ ቅርንጫፎች የሽልማት ሥነሥርዓቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በሽልማቱ የ1ኛ እና 3ኛ ዕጣ አሸናፊ አንድ ሰው መሆኑ መርኃግብሩን ልዩ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል፡፡

ባንኩ በቀጣይ ከይመንዝሩ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ መርኃግብር በተጨማሪ ለህፃናት፣ ለወጣቶች እና ለአረጋዊያን የሚሆኑ የቁጠባ መርኃግብሮችን በመዘርጋት እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ የ3ኛው ዙር ይመንዝሩ፤ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ መርኃግብር እንደምጀመርም ተጠቁሟል፡፡

በብርሃኑ አበራ