የዚምባቡዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኮቪድ19 ምክንያት አረፉ

የዚምባቡዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲቡሲሶ ሞዮ በኮቪድ 19 ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቢቆዩም ማገገም ባለመቻላቸው  ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሚዮ ሞዮንን “ታማኝ የህዝብ አገልጋይ እና እውነተኛ ጀግና” ሲሉ አድናቆታቸውን

ገልጸዋል፡፡

ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮች ኤላን ጋራዲዚምባ እና ፔርራንስ ሺሪ ባለፉት ስድስት ወራት በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉንም ዘገባው አስታውሷል።