የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

                                           የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ

የደቡብ፣ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሀዋሳ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በአንድ ቀን ውሎው የክልሉን ተጨማሪ በጀት፣ በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት ተወካይ አባላትን ብዛት ለመወሰን የወጣን አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአስፈጻሚ አካላትን ሹመትን፣ የዳኞች ሹመትና ስንብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።