የደቡብ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ ቀደም ሲል በውክልና ሲሰሩ የነበሩ የከፍተኛ አመራሮችን ሹመትም አጽድቋል።

በዚሁ መሰረትም ቀደም ሲል በምክር ቤቱ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት ተቋማትን ሲመሩ የነበሩ ነገር ግን በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ሹመታቸው ያልጸደቀ አመራሮችን ሹመት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ እርስቱ ይርዳ አቅራቢነት  ሹመቶችን ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚሁ መሰረት ፣

  1. አቶ ተስፋዬ ይገዙ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የስራና ከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ
  2. አቶ አንተነህ ፍቃዱ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ
  3. አቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
  4. አቶ አክሊሉ አግዳይ- የውሃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ
  5. አቶ ተሾመ ታከለ- የኢንተርፕራይዞችና ኢንደስትሪ ቢሮ ሃላፊ
  6. አቶ ገብሬ ዳልኬ- ሳይንስ፣ቴክኖሎጅና ኢኖቬሽን ቢሮ ሃላፊ
  7. አቶ ማሄ ቦዳ – የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ምክር ቤቱ ሹመት ሰጥቷል።

ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በሌላ በኩልም፣

  1. ወ/ሮ ፈዲላ አደም- የክልሉ ኦዲት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
  2. አቶ አባይነህ አቹላ- የክልሉ ኦዲት መስሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው እንዲሰሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር በእጩነት የቀረቡትን የተቋም ሃላፊዎች ሹመት የክልሉ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ምክር ቤቱ የቀረበለትን የስድስት እጩ ዳኞችን ሹመት ሲያጸድቅ በአሰራሩ መሰረት የስነ ምግባር ጉድለት የነበረባቸው አንድ ዳኛ እንዲሰናበቱ በክልሉ ዳኞች ጉባኤ የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበልም ዳኛው እንዲሰናበቱ ውሳኔ አሳልፏል።

በእጩ ዳኛነት ከቀረቡት 6 ግለሰቦች ውስጥ 5 ወንድና 1 ሴት ናቸው።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በተጓደሉ የቦርድ አባላት ምትክ፣

  1. አቶ ሀይለማሪያ ተስፋዬ- የቦርዱ ሰብሰቢ
  2. አቶ ተፈሪ አባተ
  3. ወ/ ሮ ሰናይት ሰለሞን
  4. ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ
  5. ወ/ሮ አስቴር ይርዳው

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦርድ አባላት ሆነው እንዲሰሩ ምክር ቤቱ ይሁንታውን  እንደሰጠ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡