የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ ይጠናቀቃል- የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።

ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የጊዜ ሰሌዳ እያወጡ እንደሚገኙ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከታህሳስ 7 እስከ 9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12 እስከ 14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ እንደሚያደርጉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡