ዩኒቨርሲቲው ለ12 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

ሰኔ 5/2016 (አዲስ ዋልታ) አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

ዩኒቨርስቲው ለምሑራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፣ ለማህበረሰብ ላበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤትን መሰረት ባደረገ ምዘና መሆኑን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት የሙሉ ፕሮፌሰርነት የተሰጣቸው ምሑራንና የትምህርት መስክ ከዚህ በታች ቀርቧል፡-

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፋርማሴዩቲክስ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በዕፅዋት ጄኔቲክስ
ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በአናሊቲካል ኬሚስትሪ
ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በዕፅዋት ባዮቴክኖሎጂ
ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን
ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በከተማ ፕላኒንግ

ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቫይሮመንታል ጥናት መሆናቸውን ከዩንቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን ሲሆኑ ይህም በአንድ ጊዜ ሁለት ሴቶች ማዕረጉን በማግኘታቸው ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል፡፡