ደቡብ አፍሪካ የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ አገደች

ደቡብ አፍሪካ የአስትራዜኒካን ክትባት ለዜጎቿ እንዳይሰጥ ማገዷን አስታወቀች፡፡

እገዳው ክትባቱ አዲሱን የኮሮና ቫይረስ በመከላከሉ ረገድ ደካማ ውጤት ማሳየቱን ተከትሎ የተጣለ ነው ተብሏል፡፡

ተመራማሪዎች ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ያካተተ ጥናት በክትባቱ ላይ አድርገው፥ ክትባቱ አዲሱን የኮቪድ19 አይነት የመከላከል አቅም አነስተኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር ዝዋሌ ምኪዝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መንግስታቸው የአስትራዜኒካ ክትባት እንዴት በተሻለ መንገድ መጠቀም እንዳለበት ተጨማሪ ምክረ ሃሳቦችን ይጠብቃል ብለዋል፡፡

እስከዚያው ግን የሃገሪቱ መንግሥት በሚቀጥሉት ሳምንታት በጆንሰን ጆንሰን እና ፋይዘር የተመረጡ ክትባቶችን ለዜጎች ይሰጣልም ነው ያሉት፡፡

ደቡብ አፍሪካ 1 ሚሊየን የአስትራዜኒካ ክትባት ከአምራቹ ወስዳ ነበር፡፡

ጥናቱን የመሩት ፕሮፌሰር ሻቢር ማዲ የአስታራዜኒካ ክትባት በአዲሱ የኮቪድ19 ተይዘው ከመለስተኛ ጀምሮ የቫይረሱን ምልክት የሚያሳዩ ሰዎችን ማከም እንደማይችል ተናግረዋል፡፡ (ምንጭ፡- ቢቢሲ)