ጊኒ ከአፍሪካ ህብረት መታገድ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) በፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ላይ የተፈፀመውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ጊኒ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች፡፡

የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ በኮሎኔል ማማዲ ዱምቡያ በሚመራው የወታደሮች ቡድን በመገልበጣቸው ጊኒ ከህብረቱ መታገዷን የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት መምሪያ በትዊተር ገፁ አስታውቀዋል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱ በክልል መሪዎች እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት፣ በተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ፣ የምዕራብ አፍሪካ የምጣኔ ሃብት ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) እና በአሜሪካ ተወግዟል።

በተጨማሪም የምዕራብ አፍሪካ የምጣኔ ሃብት ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) ከቀናት በፊት ጊኒን ከአባልነት ማገዱ ይታወሳል፡፡