ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

መጋቢት 27/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም፡-

– መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

– ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

– ግዛው ተስፋዬ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡