ጠ/ሚ ዐቢይ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ላይ ዐሻራቸውን በማሳረፍ ላይ ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቀረቡ

                                                                           ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ላይ ዐሻራቸውን በማሳረፍ ላይ ለሚገኙ አካላት ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡

“የገበታ ለሀገር ዕለት መቃረቡን በማሰብ፣ በእነዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ዐሻራችሁን በማሳረፍ ላይ ለምትገኙ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ“ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በኮይሻ፣ በወንጪ እና  በጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶችን ዲዛይን የሠሩት ቡድኖች ስፍራዎቹ ያላቸውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት በጥቅም ላይ ከማዋል አንጻር የሚደነቅ ሥራን ከውነዋል ሲሉም አክለዋል፡፡