ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ጋር

ሰኔ 01/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ጋር በመሆን በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተከሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ወንድሜ ኡሑሩ ኬንያታ የቴሌኮም ፍቃድ ስምምነትን በምንፈራረምበት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ ለማለት እወዳለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እና 1 ቢሊየን ችግኞችን ለጎረቤቶቻችን በማዘጋጀት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ወደ ቀጣናው በምታስፋፋበት ወቅት ላይ ነን ብለዋል፡፡

ይህንን መሠረት በማድረግም ከፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ጋር ችግኞችን በጋራ መትከለካቸውን አስታውቀዋል፡፡