ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኮይሻ ፕሮጀክትን ጎበኙ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሀገራዊ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን የኮይሻ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም በጅማ ከተማ የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።