ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን ባለመጉዳት ቃሏን የምትጠብቅ ናት አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሐምሌ 8/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የዓባይ ተፋሰስ እህት ሀገራትን ለመጉዳት የማታስብና ቃሏን የምትጠብቅ ሀገር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የአረብኛ መልዕክት ታማኝነት እና የገቡትን ቃል መፈጸም የኢትዮጵያዊያን በጎ ባህሪያት እና የባህላችን ዋነኛ አካል ናቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ መተማመንን ችላ የማትል እና ጎረቤቶቿን ለመጉዳት የማታስብ ሀገር መሆኗን እናረጋግጣለን ሲሉም በመልዕክታቸው አመልክተዋል፡፡

ዓባይ የላይኛውንና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ለሺህ ዓመታት ያስተሳሰረ ገመድ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው፡፡

ይህን ከፈጣሪ የተሰጠ ገጸ በረከትም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ለማልማት እና ለመጠቀም ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት አላት ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

በተጨማሪም የዓባይ ወንዝ ከልማትና ከተለያዩ ጥቅሞች ባሻገር የተፋሰሱ ሀገራት ሕዝቦችን አስተሳስሮ መቆየቱንም አስገንዝበዋል፡፡