ፍራንክ ላምፓርድ ከቼልሲ አሰልጣኝነት ተሰናበተ

ፍራንክ ላምፓርድ

አሰልጣኝ ፍራንክ ላፓርድ ከቼልሲ መሰናበቱን ቡድኑ አስታወቀ።

የቼልሲ ኮኮብ ተጫዋች የነበረው እና ቡድን ማውሪዚዮ ሳሪ የተረከበው ፍራንክ ላምፓርድ ከሃምሌ ወር 2019 ጀምሮ ክለቡን በአሰልጣኝነት ሲመራ ነበር።

ፍራንክ ላምፓርድ ከቡድኑ ጋር ላስመዘገበው ስኬታ ምስጋና አለን ያለው ቼልሲ ነገር ግን በቅርብ ጊዜያት የክለቡ ውጤት እና አቅም ከሚጠበቀው በታች ሆኗል ብሏል በመግለጫው።

ክለቡን ላለፉት 18 ወራት በአሰልጣኝነት የመራው ላምፓርድ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች አምስቱን መሸነፉን ተከትሎ ነው ስንብቱ የተሰማው።

ባለፈው የውድድር ዘመን አራተኛ ደረጃን በመያዝ ቼልሲ እንዲያጠናቀቅ ማስችላሉ በስኬት ይነሳለታል።

በዘንድሮው የዝውውር ዘመን 275 ሚሊየን ዶላር ክለቡ ወጪ ቢያደርግም በፕሪሚየር ሊጉ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤት አመርቂ አለመሆኑ ለላምፓርድ ስንብት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ጎል ዘግቧል።