ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርአት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመውን ኮሚሽን ሰበሰቡ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርአት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመውን ኮሚሽን ሰበሰቡ፡፡

ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራንንና ባለሙያዎችን ያቀፈው ኮሚሽኑ ለወደፊት ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ ትምህርት ምን መምሰል እንዳለበት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለአስተማሪዎችና ለተማሪዎች መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሪፖርት እያዘጋጀ ነው፡፡

የኮሚሽኑ አባላት እስካሁን በተሰራው ስራ ላይ የተወያዩ ሲሆን፣ ሪፖርቱ በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ይታተማል መባሉን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽኑ በፈረንጆቹ 2019 በኒውዮርክ በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መመስረቱ የሚታወስ ነው፡፡