ፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ።

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።