1ሺህ 30 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ነሐሴ 16/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 30 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 1026 ወንዶች እና 4 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ስልሳ ስምነት ሺህ 657 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡