1ሺሕ 33 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 33 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾች መካከል ስምንት ህጻናት የሚገኙ ሲሆን 1ሺሕ 25ቱ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ19ሺሕ 900 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡