125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሎስ አንጀለስ ተከበረ

የካቲት 22/2013 (ዋልታ) – በሎስ አንጀለስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በበይነ መረብ ተከብሯል፡፡

የድል በዓሉ አፍሪካውያን፣  አሜሪካውያን ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት ነው የተከበረው፡፡

በዕለቱም የታሪክ ምሁር ሰለሞን አዲስ(ዶ/ር) የጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበው  ውይይት ተደርጓል።