የከተማ አስተዳደር ካቢኔ የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ደንብ አፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ደንብ አፀደቀ፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለንግዱ ማህበረሰብ ቅሬታ አፋጣኝ ምላሽ ለመሥጠት እንዲያስችል የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን እንደገና ለማቋቋም የሚያስችል ደንብን ነው ያጸደቀው፡፡

እንደገና የተቋቋመው የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን ተገልጋዮች ከግብር አገልግሎት ጋር በተያያዘ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ ግብር ከፋዩን የሚያጉላሉ አሠራሮችን በማስቀረት ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የአደረጃጀት ለውጥም አድርጓል፡፡

በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን ዝርዝር መመሪያ የአቃቤ ህግ ቢሮ እንዲያዘጋጅ እና የታክስ አሰባሰብ እና ትመና ላይ ያለውን ቅሬታ ለመቅረፍ ኮሚሽኑ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል ነው የተባለው፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከመርካቶ እና አከባቢው ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር በተወያዩበት መድረክ ላይ ከተነሱ ቅሬታዎች መካከል አንደኛው የታክስ ትመና ሥርዓቱ ላይ ያለው ቅሬታ እንደነበር ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፡-የከንቲባ ጽህፈት ቤት)