ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፈቱ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል፡፡

በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው የተከፈቱ የልማት ፕሮጀክቶች ከ442 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደረገባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ከተመረቁ የልማት ሥራዎች መካከል 2 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ፣3 ነጥብ 1 የጠጠር  መንገድ፣ 348 አባወራዎች ሚኖሩበት እና 10 ሱቆችን  በውስጡ የያዘ የጋራ መኖሪያ ቤት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከል፣ ናማ ኮምፖስት የተሰኘ ቀሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ማዕከል፣ አቦ ፓርክ የመናፈሻ ቦታ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ተከፍተዋል፡፡

በአጠቃላይ በትላንትናው ዕለት 20 የሚሆኑ የተለያዩ የልማት ስራዎች ናቸው የተመረቁት፡፡

በተመረቁት የልማት ስራዎች ከ1 ሺህ 700 በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ተብሏል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በ2011 በጀት አመት 35 አዲስ እና 34 ነባር ፕሮጀክቶችን ከ530 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ከንቲባው አቶ መስፍን አሰፋ ተናግረዋል፡፡ (ኤፍ.ቢ.ሲ)