ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር በዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ የለውጥ ሂደቶች ዙሪያ ተወያዩ።

የዘርፉ ማሻሻያ የፋይናንስ ተቋማቱን አቅም በመገንባት የበለጠ ተፎካካሪና ብቁ ሆነው ምጣኔ ኃብትን ለማሳደግ ያላቸውን ሚና በማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ  ሚንስትሩ  ከፋይናንስ  ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር  እስካሁን ድረስ በፋይናንስ ዘርፍ የተደረጉት ለውጦች ፣ በዘርፉ ውስጥ የፖሊሲ፤ የአሠራር ሂደትና የአስተዳደር ማነቆዎችን መለየት፣  የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የፋይናንስ ዘርፉን ሚናዎችና ኃላፊነቶች በመለየት ጉዳዮች ላይ  ውይይት አድርገዋል።

የመንግስት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ረገድም ዘርፉ የሚጫወተው ወሳኝ ሚናን በተመለከተም   ጠቅላይ  ሚንስትሩ  ሌላው  የተወያዩበት አጀንዳ ነው ።

በአጠቃላይ  ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አቢይና ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ያደረጉት ውይይት ለአገር አቀፍ የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመስማማት ተጠናቋል።(ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት)