ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜን ኮሪያ መሪ የተሰማቸውን ኅዘን ገለጹ

አዲስ አበባ, ታህሳስ 13 ቀን 2004 (ዋኢማ) – የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሰሜን ኮሪያ መሪ የተሰማቸውን ኅዘን ዛሬ ገለጹ።

አቶ ኃይለ ማርያም በአገሪቱ ኤምባሲ በመገኘት በፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኢል ሞት ኀዘናቸውን የገለጹት በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ነው።

በኅዘን መግለጫው ሥነ ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደርና የኤምባሲው ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢል በ69ኛ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት ነበር።

ፕሬዚዳንቱ የሞቱት ባለፈው ቅዳሜ በባቡር ሲጓዙ ገጥሟቸው በነበረው የልብ ሕመም ምክንያት መሆኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፕሬዚዳንት ኢል መንበረ ሥልጣኑን ከሟቹ አባታቸው ኪም ኤል ሱንግ ተረክበው አገሪቱን ላለፉት 17 ዓመታት ሲመሩ እንደነበር ይታወቃል።

የፕሬዚዳንት ኢል ሥርዓተ ቀብር ታኅሣሥ 18 ቀን 2004 ይካሄዳል። (ኢዜአ)