ዋልታ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ልዩነት በማስተዋወቅ ልዩ አበርክቶ ነበረዉ -አቶ ካሳ ተክለብርሃን

ዋልታ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ልዩነት በጥናት ላይ ተመስርቶ በማስተዋወቅ ረገድ ልዩ አበርክቶ እንደነበረው የፌደራልና አርብቶአደ ጉዳዮች ሚኒስትር ገለጹ ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ 6ኛ ዓመት ክብረ በዓልና የዋልታ መደበኛ ስርጭት ጅማሮን መነሻ አድርገዉ የፌደራልና አርብቶአደ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን ከዋልታ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

አቶ ካሳ እንዳሉት የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ልዩነት በጥናት ላይ ተመስርቶ በማስተዋወቅ ረገድ ዋልታ ልዩ አበርክቶ ነበረዉ፡፡

ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች የሚኖረዉ ማህበረሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በዋልታ የተሰሩ ዘጋቢ ፊልሞች ተጨባጭ ዉጤት ያመጡ ነበር ብለዋል ሚኒሰትሩ፡፡

በዚህም ዋልታ የአርብቶአደሩ ባለውለታ እንደሆነነው ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡

በሀገርአቀፍ   ደረጃ የመገናኛ ብዙሃን ሚና አሰተዋጾ የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑን ያነሱት አቶ ካሳ ዋልታ ቴሌቭዥን ህዝብ እና መንግስት በእኩል የሚቀበሉት ሚዲያ ይሆናል የሚልእምነት አላቸው፡፡

የተቋሙን ሙያተኞችና የአመራሩን ቁርጠኝነት በቅርብ እንደሚያውቁት የተናገሩት ሚኒሰትሩ በዓለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ ዋልታ የሚጠበቅበት ውድድር ከፍተኛነው፡፡

እናም ለዚህ ፉክክር ዝግጁና ብቁ ሆኖ መገኝት እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡

አርታኢ -በሪሁ ሽፈራው