የቴፒ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በተደራጁ አካላት ቤት ንብረታቸው መውደሙንና ለስደት መዳረጋቸውን ገለጹ

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን የቴፒ ከተማ እና አካባቢው ተወላጆች የተደራጁ አካላት ቤት ንብረታቻንን አቃጥለው ለስደት  እንድንዳረግ  እያደረጉን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን  ለዋልታ አቅርበዋል ፡፡

 የተደራጀ ቡድን የመንግስት ተሽከርካሪዎችንም ጭምር በመጠቀም በአካባቢያቸው አመጽ እየቀሰቀሰ መሆኑን የጠቀሱት ነዋሪዎቹ  ያለአግባብ ለወደመባቸው ንብረት መንግስት ካሳ ሊከፍላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው በስልክ  የጠይቀው  በሠጡት ምላሽ እንደገለጹት በተለይ በቴፒ ከተማና በየኪ ወረዳ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ካቆሙ ከአራት ወር በላይ መቆጠሩን ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው ግጭት አነሳስተዋል የተባሉ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው አሁን ላይ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጎ ተቋማቱ አገልግሎት መሥጠት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው የሚገኘው ዩንቨርሲቲም በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ ሥራውን እንደሚጀምር አቶ የሸዋስ ገልጸዋል፡፡