“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው

"የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው፡፡

ኮንፈረንሱን የሰላም ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋራ ነው ያዘጋጁት፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እየተሳተፋ ይገኛሉ። (ምንጭ፡-የሰላም ሚኒስቴር)