በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን በማገልገል ላይ የሚገኙ ዲፕሎማቶች እንጦጦንና የተለያዩ ቦታዎችን እየጎበኙ ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ  አገራት  ኢትዮጵያን በማገልገል ላይ የሚገኙ አምባሳደሮችን የተለያዩ የአዲስ  አበባ  ታሪካዊ ቦታዎችን እንዲጎበኙ  እያደረገ  መሆኑ ተገለጸ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህል ዲፕሎማሲ ቀንን በማስመልከት ነው  በአዲስ  አበባ  የተለያዩ  ሥፍራዎች ላይ ጉብኝት ማዘጋጀቱን ጠቅሷል።

 በጉብኝቱ  ወቅት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳታፊ ነበሩ ።

አምባሳደሮቹ በጉብኝቱ ወቅት የባህል ዲፕሎማሲ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦን  አንስተዋል።

አምባሳደሮቹ ጉብኝታቸውምበእንጦጦ የአፄ ሚኒሊክና እቴጌ ጣይቱ መታሰቢያ ቤተ መዘክርን ጎብኝተዋል።

መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አምባሳደሮችን የተለያዩ ቦታዎችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።