ኢትዮጵያና ሴራሊዮን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሴራሊዮን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሰራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

መሪዎቹ በማዕድን፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ውጤታማ የሚባል ውይይት አድርገዋል፡፡

በተደረገው የሁለትዮሽ ውይይትም በሁለቱ አገራት መካከል በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ አንድ አጠቃለይ ስምምነት እና አንድ የመግባቢያ ስምምነት በድምሩ ሁለት ስምምነቶች ተፈርመዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተመራው የመንግስት ልኡካን ቡድን ውስጥ የማዕድን ሚኒስትር እና የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሰልጣናት ተካተዋል ነው የተባለው፡፡ (ምንጭ፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)